Main Article Content

የታክስ ከፋዮች ቅሬታ Aፈታት ሥርዓት በIትዮጵያ


Aስቻለው Aሻግሬ

Abstract

በማንኛውም ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት ውስጥ በታክስ Aስገቢው ባለሥልጣንና በታክስ ከፋዮች መካከል ልዩ ልዩ Aለመግባባቶች Eንደሚከሰቱ Eሙን ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የታክስ ሥርዓት Eነዚህ Aለመግባባቶች የሚፈቱባቸው ሕጋዊና ተቋማዊ ማEቀፎችን መዘርጋትና ሥራቸውን በትክክል Eንዲሠሩ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በEኛ ሀገርም ዘመናዊ የታክስ ሕጎች ከታወጁበት ጊዜ ጀምሮ Eስካሁን ድረስ በታክስ Aስገቢው ባለሥልጣንና በታክስ ከፋዮች መካከል የሚነሱ Aለመግባባቶች የሚስተናገዱባቸው የሕግና የተቋማት ማEቀፎች ተዘርግተዋል፡፡ የዚህ Aጭር ጽሑፍ ዋና ዓላማ Aሁን በIትጵያ ተግባራዊ የተደረጉት የታክስ ከፋዮች ቅሬታ Aፈታት ሥርዓቶች የታክስ ከፋዩን ቅሬታዎች Aስተማማኝና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማስተናገድ፣ የታክስ ከፋዩን የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት መብት በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆን Aለመሆናቸውን መመርመር ነው፡፡ ይህ ጸሐፊ በዚህ የምርምር ሥራ Eንደተገነዘበው በIትዮጵያ ውስጥ የተዘረጉት የታክስ ከፋዮች ቅሬታ የሚፈቱባቸው ሥርዓቶች ለታክስ Aስገቢው ባለሥልጣን ጥቅም ያደሉ በመሆናቸው የታክስ ከፋዩን ቅሬታዎች ፍትሐዊ በሆነ መልኩ በማስተናገድ የታክስ ከፋዩን ፍትሕ የማግኘት መብት በAስተማማኝ ሁኔታ የሚያረጋግጡ Aይደሉም፡፡ በመሆኑም Eንደዚህ ፀሐፊ Aመለካከት የታክስ ከፋዩን የመሰማትና ፍትሕ የማግኘት የማይገሰስ መብት ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማረጋግጥ ሚዛናዊ የሆነ የታክስ ቅሬታ Aፈታት ሥርዓት መዘርጋት Aስፈላጊ ስለሆነ Aሁን ያለውን የታክስ ከፋዮች ቅሬታ Aፈታት ሥርዓት Eንደገና መፈተሽና ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡

ቁልፍ ቃላት ታክስ፣ ግብር፣ ታክስ ከፋይ፣ የታክስ ከፋይ ቅሬታ፣ የታክስ ከፋይ ቅሬታ Aፈታት፣ Aጣሪ ኮሚቴ፣ የግብር ይግባኝ ጉባኤ፣ ይግባኝ፣ የሕግ ስህተት፣ የማስረዳት ሸክም፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2309-902X
print ISSN: 1998-9881