Main Article Content

Growth, Yield, and Fruit Quality Performance of Peach Varieties


Kidest Firde
Habtam Setu
Tenagne Eshete
Tajebe Mosie
Getaneh Sileshi
Edeo Negash

Abstract

አህፅሮት
ይህ ጥናት የተካሄደው ከውጪ የገቡ ስድስት የኮክ ዝርያዎችን ማክሬድ የተባሇውን ቀደም ሲል ገብቶ በመመረት ላይ ያሇ ዝርያን እንደ ማወዳደሪያ በመጠቀም በደጋማ የሀገሪቱ ክፍል በተሇይም በሆሇታና አካባቢው ያላቸውን የዕድገት፣ ምርት እና ጥራት ሁኔታ ሇመገምገም ነው፡፡ እያንዳንዱ ዝርያ ሶስት ጊዜ በተሇያየ ረድፍ ተተክሇው አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው አድገዋል፡፡ የተገኘው መረጃ እንደሚያመሇክተው እ.ኤ.አ 2006 እና 2007 ዓ.ም በስተቀር በዛፉ ቁመት ላይ ምንም አይነት ልዩነት አሇመኖሩን ሲሆን ትሮፒክ ቢዩቲ፣ 9A-35C፣ ማክሬድ፣ 88-18W እና 90-19H የተባለት ዝርያዎች የተሻሇ ቁመት አስመዝግበዋል፡፡ በተጨማሪም እ.ኤ.አ ከ 2010 ዓ.ም በስተቀር ሁለም ዝርያዎች ተመሳሳይ የቅርንጫፍ ስፋት አሳይተዋል፡፡ መረጃው እንደሚመሇክተው የግንድ ውፍረትን በተመሇከተ በዝርያዎች መካከል መረጃ በተወሰደባቸው አመታት በሙለ ልዩነት አሳይተዋል፡፡ በዚህም መሰረት ትሮፒክ ቢዩቲ እና 90-19H ከሌሎች ዝርያዎች የተሻሇ የግንድ ውፍረት አስመዝግበዋል፡፡ አማካይ ሇሽያጭ የሚቀርብና ጠቅላላ ምርት እንዲሁም ከአንድ ዛፍ ላይ በሚገኝ የፍሬ ቁጥር እና አማካይ የፍሬ ክብደት ላይ በዝርያዎች መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተመዝግቧል፡፡ ዝርያዎቹ እድሜአቸው እየጨመረ ሲሄድ የምርት መጠናቸውም እንደሚጨምርና ያላቸውን የምርት አቅም እንዳሳዩ ሇመረዳት ተችሏል፡፡ በተገኘው መረጃ መሰረት የትሮፒክ ቢዩቲ አማካይ ጠቅላላ ምርት 110.4 ቶን በሄ/ር ሲሆን የ90-19H ኤች ደግሞ 89.67 ቶን በሄ/ር ነው፡፡ እነዚህ ዝርያዎች ከማወዳደሪያ ዝርያው (ማክሬድ) የ 45 እና 32% ብልጫ አሳይተዋል፡፡ ከአንድ ዛፍ ላይ የሚመረት አማካይ የፍሬ ቁጥር 90-19H፣ ትሮፒክ ቢዩቲ እና 88-22C ከሌሎች የተሻሇ ሲሆን የፍሬ ክብደታቸው ደግሞ በተከታታይ 78.12፣ 76.06፣ እንዲሁም 76.06 ነው፡፡ የድህረ-ምርት ጥራትን በተመሇከተ በጠቅላላ ስኳርና የአሲድ መጠን፣ የፍሬ ዲያሜትር እንዲሁም የብስሇት አመላካች መረጃ ላይ ልዩነት ተመዝግቧል፡፡ በመሆኑም የ9A-35C ጠቅላላ የስኳር መጠን 13.67% ሲሆን የ88-18W የአሲድ መጠን 1.03% ከሌሎቹ ዝርያዎች ሲነጻጸር ከፍተኛ እንደሆነ ሇመረዳት ተችሏል፡፡


Abstract
The study was conducted to evaluate peach varieties for their growth, yield and quality performance under Holetta condition. The treatments consisted of six peach varieties including McRed (standard check). The trial was laid in randomized complete block design with three replications. The result indicated statistically similar tree height across the growing seasons except in 2006 and 2007. Tropic beauty, 9A-35C, McRed, 88-18W and 90-19H showed better plant height in their order. All varieties had statistically significant parity in canopy spread in all growing seasons except in 2010. However, there was a significant difference in trunk cross-sectional area across all seasons. Tropic beauty and 90-19H exhibited better trunk cross-sectional area. Highly significant differences in mean marketable and total fruit yield, fruit number per tree and average fruit weight were observed. The mean total fruit yields of Tropic beauty and 90-19H were 69.03 and 56.23 t ha-1, respectively. These varieties had 45.0 and 32.5% yield advantage over the standard check, McRed. Moreover, varieties 90-19H, Tropic beauty and 88-22C had better mean fruit numbers per tree and fruit weight (78.12, 76.06, and 76.06 g in the aforementioned order) as compared to others. In terms of fruit quality, there were significant differences among varieties regarding total soluble solids, titratable acidity, fruit diameter, and ripening index. Variety 9A-35C has the highest TSS (13.67%) while variety 88-18W has the highest TA (1.03%) and fruit diameter (5.76 cm) and followed by Tropic beauty (0.95% and 5.46 cm, respectively). Variety 90-19H exhibited superior ripening index and the least was obtained from 88-18W.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605