Main Article Content

Major Insect Pests and their Associated Losses in Quantity and Quality of Farm-Stored Wheat Seed


Karta Kaske Kalsa
Bhadriraju Subramanyam
Girma Demissie
Admasu Fanta Worku
Nigus Gabbiye Habtu

Abstract

አህጽሮት
በተከዘነ ስንዴ ላይ በጎተራ ነፍሳት ሰበብ ጉልህ ብክነት ይደርስ ወይም አይደርስ እንደሆነ ብዙ ክርክር አሇ፡፡ የችግሩን አገር አቀፋዊ ይዘት ሇመረዳት ከአማራ፣ ከኦሮሚያ፣ ከደብብህ፣ እና ከትግራይ ክልሎች በተመረጡ አምስት የስንዴ አብቃይ ወረዳዎች ላይ የስንዴ ናሙናዎችን ከአርሶ አደር መጋዘኖች በመሰብሰብ የዳሰሳ ጥናት እ.አ.አ. በ2016 በሰኔ ወር ተከናውኗል፡፡ ከእናንዳንዱ አርሶ አደር ቤት አንድ ኪሎግራም በመውሰድ በድምሩ 150 ናሙናዎች ተሰብስበው ተፈትሸዋል፡፡ ከናሙናዎቹ ላይም የጎተራ ነፍሳት አይነቶች፣ በነፍሳት ምክንያት የደረሰ የክብደት መቀነስ በመቶኛ፣ በነፍሳት ምክንያት የደረሰ የመቦርቦር ችግር እና በመጨረሻም የዘር ብቅሇት ደረጃ መረጃዎች ተሰብስበው ተተንትነዋል፡፡ በተገኘው መረጃ መሰረት ከስድስት ያላነሱ የጎተራ ነፍሳት አይነቶች የታዩ ሲሆን በነፍሳት የተበሳ/የተቦረቦረ የስንዴ ፍሬ ቁጥር በየወረዳው በአማካይ በመቶኛ ከ3.6 እስከ 13.6 መሆኑ ታይቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በነፍሳት ምክንያት በዘር ላይ የደረሰ የክብደት መቀነስ በየወረዳው በአማካይ በመቶኛ 1.5 ነበር፡፡ በተጨማሪም አማካይ የዘር ብቅሇት በአማካይ በመቶኛ 72.3 ብቻ ሆኖ ታይቷል፡፡ በአሁኑ የዳሰሳ ጥናት ውጤት መሠረት በአርሶ አደሮች በተከዘነ የስንዴ ዘር ላይ በጎተራ ነፍሳት ምክንያት የሚደርሰው ጉዳት በዓይነትም በጥራትም ረገድ ከተጠበቀው በላይ መሆኑን ሇመረዳት ይቻላል፡፡ ስሇዚህም አግባብነት ያላቸው የተከዘነ ስንዴ መጠበቂያ አሰራሮች ሇአርሶ አደሮች መተዋወቅና በክዘና ደረጃ የሚደርሰውን ብክነት የመቀነስ ሥራ መሠራት አሇበት፡፡


Abstract
There is considerable debate over the importance of losses associated with insect pests of stored wheat at the farm level in Ethiopia. A survey was conducted to assess the most significant insects and losses of farm-stored wheat in five districts in Amhara, Oromiya, Southern Nations, Nationalities and Peoples, and Tigray regional states of Ethiopia during 2016. One kg samples of stored wheat seed were collected over a period of eight months from 150 farmers. The samples were kept in the laboratory for approximately six weeks to allow the population of insects present to develop and emerge as adults. After adult emergence, the resultant weight loss, seed damage, and loss of seed germination were determined. Major primary insect pests identified were the granary weevil, Sitophilus granarius, Sitophilus spp., and the Angoumois grain moth, Sitotroga cerealella. Secondary pests such as Tribolium spp., the India meal moth, Plodia interpunctella, and Liposcelis spp. were detected in a few samples. Wheat experienced mean percentage kernel damage that ranged from 3.6 to 13.6%. Mean weight loss due to insects was 1.5%, while mean seed germination was only 72.3%. The present survey indicated that farmers are incurring a considerable loss in the quantity and quality of stored wheat due to insects. Hence, there is an urgent need to devise appropriate tactics for protecting the losses in farm-stored wheat in Ethiopia.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605