Main Article Content

Emerged Plant Virus Disease in Ethiopian Agriculture: Causes and Control Options


Adane Abraham

Abstract

አህፅሮት
ባሇፉት ሁሇት አሰርት ዓመታት በርካታ እንዯአዲስ የተከሰቱ ወይም ቀድሞ የነበሩ ነገር ግን ስርጭታቸውን ያሰፉ የዕጽዋት ቫይረስ በሽታዎች ከፍተኛ የሰብል ምርት ብክነት በማድረስ በኢትዮጵያ ግብርና አለታዊ ተጽዕኖ እያዯረጉ ይገኛለ፡፡ ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋና የሆኑት ስምንቱ በሽታዎች የበቆሎ አድርቆ ገዳይ፤ የስኳር ድንች አቀጫጭ፤ የትምባሆ አናት ጨምዳጅ፤ የቲማትም ቅጠል ብጫ አድራጊ የጥራጥሬ አቀጫጭ፤ የባቄላ ብጫ ገዳይና አቀጫጭ፤ የእንሰት ቅጠል ስቲሪክና የጎመን ሞዛይክ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለም በሽታዎች በመስክ በተሇያዩ ነፍሳት ተባዮች አማካይነት የሚተላሇፉ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ሶስቱ ማሇትም የበቆሎ አድርቆ ገዳይ፤ ስኳር ድንችና የትምባሆ ቫይረስ በሽታዎች ቢያንስ በሁሇት የተሇያዩ ቫይረሶች በጋራ ሰብለን ሲያጠቁ የሚከሰቱ ሲሆን ሌሎቹ አምስት በሽታዎች በአንዳንድ ቫይረስ ብቸኛ ጥቃት የሚመጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከቫይረሶቹ መካከል አምስቱ ሇመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተገኙ ሲሆኑ በሀገሪቱ ሇዘመናት ከሚያጠቋቸው መጋቢ ሰብሎች ጋር ተላምዶ የኖሩ እንዯሆኑ ይገመታል፡፡ በሌሎች ሀገሮች እንዳለ የሚታወቁት ሜይዝ ክሎሮቲክ ሞትል ቫይረስ የመሳሰለት ዯግሞ የሰብሎች ዘሮች ሇምርምር ወይም ሇንግድ እንቅስቃሴ ሲባል ወዯሀገሪቱ ሲገቡ አብሮ እንዯገቡ ይገመታል፡፡ ስሇበሽታዎቹ መንስኤና በመስክ ስሇሚሰራጩበት መንገድ በቂ መረጃ ሲኖር የሚያዯርሱትን ብክነት ሇማስቀረት በሌሎች ሀገሮች ስራ ላይ የዋለ የመቆጣጠሪያ ስልቶች መጠቀም የሚቻል ሲሆን እነዚህም በዚህ ወረቀት ተጠቃሎ ቀርቧል፡፡ ቁጥጥሩን በይበልጥ ውጤታማና ዘላቂ ሇማድረግ ግን የተከሰቱበትን ስነ ምህዳርና አከባቢያዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ጥናትና ምርምር ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተከሰቱትን የቫይረስ በሽታዎችን በሀገር ዯረጃ በአስተማማኝነት ሇመቆጣጠርና አዋጭ የሆኑ ስልቶች ሇገበሬው በማቅረብ ላይ የሚታይ ጉልህ ክፍተት አሇ፡፡ በመሆኑም እየዯረሰ ያሇውን የምርት ብክነት ሇማስቀረት ሀገር-አቀፍ የሆነ የተቀናጀ የሰብል ቫይረስ በሽታዎችን ሇመቆጣጠር የሚያስችል የምርምርና ሥርጸት ፕሮገራም በመቅረጽና ሇአፈጸጸሙ እስፈላጊዎቹን ግብዓቶችን ሁለ በማቅረብ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡

Abstract
Many plant virus diseases that have either newly emerged or expanded their distribution in the last two decades are causing tremendous crop losses to Ethiopian agriculture. The eight most significant of these are maize lethal necrosis (MLN), sweet potato virus (SPV), tobacco bushy top (TBT), tomato yellow leaf curl, legume stunt, faba bean necrotic yellows and stunt, enset leaf streak and cabbage mosaic diseases. MLN, SPV and TBT diseases are caused by synergistic interaction of at least two viruses while others are caused by single virus infection. Insect vectors transmit all the causal viruses. Five of the viruses involved namely Chickpea chlorotic stunt virus, Enset leaf streak virus, Ethiopian tobacco bushy top virus, Faba bean necrotic stunt virus and Faba bean yellow leaf virus are described and reported for the first time from Ethiopia. These new viruses have likely co-evolved with their hosts in Ethiopia. On the other hand, viruses previously known elsewhere such as Maize chlorotic mottle virus may have been introduced to the country by either germplasm import, seed trade or other means. If the causal virus and its mode of field spread are understood, disease control practices used elsewhere can be adapted and recommendation can be made accordingly. However, for efficient and sustainable management based on integrated approach, local studies on epidemiological parameters are necessary.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605