Main Article Content

The Prevalence of Fish Parasites of Nile Tilapia (Oreochromis niloticus) in Selected Fish farms, Amhara Regional State


Marshet Adugna

Abstract

አህፅሮት


የዚህ ጥናት ዓላማ በአማራ ክልል በተመረጡ የዓሳ ግብርና በሚሰራባቸው አካባቢዎች የቆሮሶ ዓሳ ጥገኛ በሽታዎችን ለመለየት እና ሽፋናቸውን ለማወቅ የተካሄደ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ሦስት አነስተኛ መጠን ያላቸው የግል ዓሳ ርባታ ማዕከላት እና አንድ በመንግስት ስር ያለ የዓሳ ዘር ማባዣ ማዕከል በጥናቱ ተካተዋል፡፡ የቆሮሶ ዓሳ ናሙናዎችም ከተመረጡት የዓሳ ኩሬዎች ውስጥ የተሰበሰቡ ሲሆን ወደ ባህር ዳር ዓሳ እና ሌሎች የውሃ ውስጥ ሕይወት ምርምር ማዕከል ላብራቶሪ ተወስደው ምርመራ ተደርጓል፡፡ የጥገኞች ዓይነትም በፓራሲቶሎጅ ላብራቶሪ ሂደቶች እና የመለያ ቁልፎች በመጠቀም ልየታ ተደርጓል። በዚህ መሠረት ስምንት ዓይነት ጥገኞች ማለትም ክሊኖስትቶመም፣ ዲፕሎስቲም፣ ኒያስከስ፣ ኮንትራሴከም፤ ሲክልዶጋይረስ፣ አክንቶሴፋላ፣ አርጉለስ፤ እና ትራይኮዲና የተባሉ ተለይተዋል፡፡ ከተሰበሰቡት 198 ናሙናዎች መካከል 73.20 በመቶ ዓሳዎች በተለያዩ ውጫዊ እና ውስጣዊ ጥገኛ ተህዋሲያን የተያዙ ሲሆን ከዓሳዎቹ 48.3 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አንድ እና ከዚያ በላይ በሆኑ የጥገኛ ተህዋሳት የተያዙ ናቸው፡፡ በክልሉ ውስጥ የዓሳ ጥገኞችን ቦታ እና ጊዜን መሠረት በማድረግ እንዲሁም ህይወት ያላቸው እና የሌላቸው አባባሽ ሁኔታዎችን በማካተት ተጨማሪ ጥናቶች ሊደረጉ ይገባል፡፡


 


Abstract


This study was conducted to assess the prevalence of fish parasites collected from selected small-scale fish farms in selected zones of Amhara regional state.  Three small scale private fish farms and one government owned fish seed multiplication farm were considered in this study. Nile tilapia (Oreochromis niloticus) samples were collected from selected fish ponds in using seine nets and were transported live to the Bahirdar Fishery and Other Aquatic Life Research Center laboratory. Parasites were identified to the genera level with parasitological laboratory procedures and identification keys. Accordingly, eight genera of fish parasites belonging to trematodes (Clinostomum spp, Diplostomum spp., and Neascus), nematode (Contracaecum spp.), monogenea (Cichlidogyrus spp.), Acanthocephala spp., crustacean (Argulus spp.) and protozoan (Trichodina spp.) were identified. Among 198 the sampled fish, 73.20% of the fish were infected by different external and internal parasites and 48.3% of the fish were infected by mixed parasite infections. Further studies of fish parasites in the region should be done considering spatial and temporal or biotic and abiotic factors in disease causations in aquaculture.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605