Main Article Content

Fodder Yield and Nutritive Values of Hydroponically Grown Local Barley Landraces


Bonsa Bulcha
 Diriba Diba
Geleta Gobena

Abstract

አህፅሮት


በዋነኛነት በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ብዛት ለመመገብ በመሬት ላይ ባለው ጫና ምክንያት ከፍተኛ የመኖ ምርትን በቀላሉ ዕውን ማድረግ አልተቻለም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የአረንጓዴ መኖ ፍላጎት ለማሟላት አማራጮች አንዱ ሃይድሮፖኒክ (መኖን ከአፈር ይልቅ በውኃ ማብቀያ ዘዴ) መጠቀም  ነው። በሦስት ሀገር በቀል ገብስ ዘሮች ማለትም ጥቁር፣ ሞስኖ እና ነጭ ገብስ የተለያዩ  የውኃ ማጠጣት ሰዓታት ልዩነት፣ የመከር መሰብሰብ ቀን ልዩነትና የዘር ልዩነት በምርት እና ንጥረ-ነገር ይዘቶች ላይ የሚያደርሱትን ተፅዕኖ ለመገምገም ጥናት ተካሂዷል። ሦስቱም ሃገር በቀል የገብስ ዝርያዎች 12 ተከታታይ ቀናት በሙከራ ቤት (ላት ሃዉስ) 2 3 እና 4 የውኃ ማጠጫ ሰዓታት ልዩነት በቅለዋል። መኖው የታጨደዉ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 10 እና 12ኛው የዕድገት ቀን ነው። የመከር መሰብሰብያ  ቀናት ልዩነት በመኖ ምርትና ተያያዥነት ያላቸው የምርት ክፍሎች  መካከል ከፍተኛ ልዩነቶችን ፈጥሯል። ከፍተኛው የመኖ ዕድገት ከተዘራ 12ኛው ቀን ታይቷል፣ ከፍተኛው የደረቅ ቁስ ምርት ግን 6ኛው የዕድገት ቀን ተመዝግቧል። የጥቁር፣ ሞስኖ እና ነጭ ገብስ አማካይ የደረቅ ቁስ ምርት በቅደም ተከተል 23.3ቶንሄክታር፣ 18.78 ቶንሄክታር እና 19.85ቶንሄክታር ነዉ፡፡ የክሩድ  ፕሮቲን እና የሴል ዎል ይዘቱ ለበቀለ ገብስ ከእህሉ ከፍ ያለ ነው። የገብስ እህል ደረቅ ቁስ ይዘት 93.6በመቶ ሲሆን 12 ቀን ወደ 91.7በመቶ ቀንሷል። የበቀለ ገብስ የተሰበሰበበት 6ኛው ቀን እንቪትሮ ዽራይ ማተር ይዘት ከፍተኛ ውጤት ያስገኛል ምክንያቱም ገና የበቀለበት ደረጃ ላይ ስለነበር እና ብዙ ያልበቀለ እህል ስላለው። የክሩድ ፕሮቲን  ይዘቱ እየጨመረ የመጣ አዝማሚያ ነበረው እና 12ኛው ቀን መሰብሰብ ከፍተኛ ሆኖ ታይቷል። ስለዚህ ሞስኖ ለሚባል የአገባኒ ገብስ ዓይነት ከፍተኛው የቅጠላማነት ባዮማስ ምርት እና ምርትን ተዛማጅ ክፍሎች መገኘቱን መደምደም ይቻላል። 12ኛው ቀን የመኸር መሰብሰብያ ከፍተኛ የሃይድሮፖኒክ መኖ ምርትና ጥራት ለማግኘት በአካባቢው የገብስ ዘሮችን ለመሰብሰብ አመቺ ጊዜ እንደሆነ ተለይቷል። የበቀለ ሀገር በቀል ገብስ ዘሮች ከፍተኛ የክሩድ  ፕሮቲን እና የሴል ዎል ይዘቶች ሲኖራቸው ያልበቀለው የገብስ እህል ተጓዳኝ ግን ትንሹን ይይዛል። ስለዚህ ከተዘራ በኋላ 12ኛው ቀን የሚታጨደዉ ጥቁር ገብስ በዚህ ሙከራ መሠረት በአካባቢው ከሚገኙ የገብስ ዘሮች መካከል በሃይድሮፖኒክ (መኖን ከአፈር ይልቅ በውኃ ማብቀያ ዘዴ) ለማምረት ይመከራል። ለወደፊትም እንስሳትን በመመገብ ተጨማሪ ሙከራ ተሠርቶ የወተት ይዘቱን፣ የሥጋ ምርቱን እና/ወይም የምጣኔ ሀብት ጠቀሜታዉን ማየት ቢቻል መልካም ነዉ ተብሎ  ይመከራል፡፡


 

 


Abstract

Significant fodder production cannot easily be realized mainly due to the pressure on land for the production of staple food crops to feed the ever increasing human population in Ethiopia. To meet the parallel increasing demand for green fodder, one of the alternatives is hydroponic fodder to supplement the meager pasture resources. A study was conducted at Wollega University to evaluate the effect of watering interval, harvesting dates and landraces on fodder yield and nutritive values of three local barley landraces viz: black barley, Mosno, and white barley under hydroponic systems. All three landraces were grown for 12 consecutive days in lath house at 2, 3 and 4h watering intervals. The fodder was harvested at 6th, 8th, 10th and 12th days of growth. There were significant differences (P<0.05) among dates of harvesting on hydroponic fodder yield and yield related components of all the landraces. The highest fodder growth was observed at 12th days after sowing, whereas the highest dry matter (DM) yield was recorded at the 6th day of growth. The average dry matter yield for the landraces was 23.3t/ha, 18.78t/ha and 19.85t/h2 for black barley, Mosno and white barley, respectively. The crude protein (CP) and cell wall contents were higher for sprouted barley landraces than its grain.  The DM content of the barley grain was 93.6% and decreased to 91.1% for sprouted barley on the 12th day of harvesting. The 6th date of harvesting of sprouted barley resulted in higher In vitro-dry matter digestibility. The CP content had an increasing trend and remained highest on 12th day of harvesting. Therefore, it can be concluded that watering at 4h intervals had resulted in the highest biomass yield and yield related components of barley grown under a hydroponic system. Among the landraces used in this experiment, Mosno was found to be best variety for green fodder biomass yield and as well for better nutritive values. The 12th date of harvesting was identified as an optimum time of harvesting for the highest hydroponic fodder yield and yield related components. Sprouting barley had highest CP, cell wall contents (NDF, ADF and ADL) and ash contents compared to its grain counterpart. The IVDMD and DM percentage were higher in barley grain than sprouted barley fodder landraces. Watering at 4 h interval and harvesting at 12th day could be recommended for applications for the production of optimum fodder with better nutritive values from hydroponically grown barley. On the basis of this finding, it is also very important to undertake feeding experiments to see dairy performances of cows and/or other feeding trials for evaluating animal performances and economic returns.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605