Main Article Content

Integrated Control of the White Mango Scale Through Tree Management and Soil Drenching with a Systemic Insecticide in Western Ethiopia


Belay Habtegebriel
Dawit Melisie
Teshale Daba
Tesfaye Hailu
Ferdu Azerefegn

Abstract

አህፅሮት


ነጭ የማንጎ ስኬል ሰይንሳዊ መጠሪያው Aulacaspis tubercularis (Hemiptera: Diaspididae) ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. ተከስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የማንጎ ምርትን አደጋ ላይ የጣለ ተባይ ነው፡፡ በመላው አገሪቱ በአጭር ጊዜ ተሰራጭቶ የማንጎ ምርትና ጥራት እንዲቀንስ አድርጓል፡፡ ተባዩን ለመቆጣጠር ከሚወሰዱ ርምጃዎች ውስጥ፤ ፀረ-ተባይ መጠቀም፣የተክል አያያዝን ማሻሻልና በጥገኛ ነፍሳት በመጠቀም በሥነ-ሕይወታዊ መንገድ መቆጣጠር ይገኙበታል፡፡ በማንጎ ተክል ውስጥ ተሰራጭቶ የሚሰራ ፀረ-ተባይን በአንድ ሊትር ውሀ በጥብጦ በተክሉ ዙሪያ ማጠጣትና የማንጎን ቅርንጫፎች መግረዝ (የተክል አያያዝን መጠቀም) ነጭ የማንጎ ስኬል ተባይን ለመቆጣጠር ያለውን ፍቱንነት ለመመርመር እ.ኤ.አ. በ2018 እና 2019 ዓ.ም. በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ሁለት አካባቢዎች ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የመስክ ሙከራ ተካሄዶ ነበር፡፡ ለሙከራው በሶስት ድግግሞሽ የተሰራ ራንደማይዝድ ኮምፕሊት ብሎክ የተባለ ዲዛይን ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በውጤቱም የተባዩ ድምር ቁጥር በሁለቱም ዓመታትና በሁለቱም አካባቢዎች ማለትም ኡኬ እና ባኮ ላይ ውጤታማ በሆነ መልኩ ሊቀንስ ችሏል፡፡ ኡኬ ላይ የማንጎ ተክል ቅርንጫፎችን መግረዝና ቲያሜቶክሳም 25በመቶ WG 18ግራም በአንድ የማንጎ ተክል ዙርያ በአንድ ሊትር ውኃ በጥብጦ መርጨት በመጀመሪያው ዓመት የመጀመሪያ ርጭት ወደ ዝቅተኛ የተባዩ ቁጥር (42.23 በቅጠል) ሲያወረደው በዚያው ዓመት ሁለተኛው ዙር ርጭት ወደ 27.83 በቅጠል አድርሶታል፡፡ ይህንኑ ፀረ-ተባይ በተመሳሳይ ሁኔታ በ12 ግራም መጠን መስጠት ደግሞ የተባዩን ቁጥር በመጀመሪያ ዙር ርጭት 86.83 በቅጠል እንዲሆን ሲያደርገው በሁለተኛው ዙር ርጭት ወደ 61.0 በቅጠል እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡ ለማወዳደሪያ ምንም ርጭትም ሆነ መግረዝ ያልተደረገባቸው የማንጎ ተክሎች በመጀመሪያው ዙር ርጭት 334.32 ተባይ በቅጠል እንዲሁም በሁለተኛው ዙር ርጭት 591.29 ተባይ በቅጠል የሆነ ከፍተኛ ቁጥር ታይቶባቸዋል፡፡ ባኮ ላይም የተካሄደው ሙከራ ተመሳሳይ ውጤት አሳይቷል፡፡ይህ ምርምር ከላይ የተጠቀሰውን ዘዴ መጠቀም ተባዩን ለመቆጣጠር ተስፋ ሰጪ ውጤት ያስገኘ መሆኑን አመላክቷል፡፡ ይህንኑ ዘዴ ከሌሎች ማለትም ጥገኛ ነፍሳትን በመጠቀም በሥነ-ሕይወታዊ መንገድ መቆጣጠር ዘዴዎች ጋር ማቀናጀት ያለውን ጠቀሜታና ፀረ-ተባዩ በማንጎ ፍሬ ይዘት ላይ ያለውን ተፅዕኖ በቀጣይ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡


 


Abstract


The white mango scale insect, Aulacaspis tubercularis (Hemiptera: Diaspididae) is a recent threat to mango production in Ethiopia which was introduced in 2010. It has spread to all mango producing areas of the country within a short period of time reducing the production and quality of mangos. Control measures taken against the white mango scale include the use of chemical insecticides, cultural practices and biological control using parasitoids and predators. Field experiments were conducted in western Ethiopia in two locations for two consecutive years in 2018 and 2019 to evaluate the efficacy of integrated application of a systemic soil drenching pesticide and tree management (pruning) for the control of the white mango scale. Randomized complete block designs with three replications were used for the experiments. The total number of WMS life stages varied significantly among the different treatments throughout the two years and application seasons at both Uke and Bako sites.  At Uke Thiamethoxam 25% WG at 18g/tree + pruning treated trees showed the minimum mean number of WMS life stages per leaf (42.23) and (27.83) followed by Thiamethoxam 25% WG at 12g/tree + pruning treated trees (86.83) and (61.0) in the first and second application seasons respectively. Control trees showed the highest (334.33) and (591.29) number of WMS life stages in the first and second application seasons respectively. Similar trends were observed at Bako. The study has shown that the integrated use of the systemic soil drenching insecticide and tree management can significantly reduce the WMS life stages on infested mango trees indicating that it is a promising approach to the control of the WMS. Integration of these approaches with other management components such as biological control agents and the effect of the systemic insecticide on the content of the edible fruit deserves further study.


 


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605