Main Article Content

Growth and Fattening Performances of Friesian-Boran Crossbred Bull Calves Fed on Different Protein Supplements


Molla Shumye
Zewdie Wondatir
Getu Kitaw
Aemiro Kahaliw

Abstract

አህፅሮት


50 እና 75 በመቶ የሆልስቴን ፍሬዥያን ዝርያ ደም ያላቸው  ወተት መመገብ ያቆሙ የዲቃላ ወንድ ጥጆችን የዕድገት ብቃትንና በወይፈንነት ዕድሜያቸው የማደለብ ኢኮኖሚያዊ አዋጪነትን ለመገምገም በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ 626 ቀናት ያህል ጥናት ተካሂዷል፡፡ ለዚሁ ጥናትም ሃያ አራት 50 በመቶ እና ሌሎች ሃያ አራት 75 በመቶ የሆልስቴን ፍሬዥያን ደም ያላቸውን ጥጆች በስድስት የአመጋገብ ስርዓት (Treatments) እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡ የአመጋገብ ስርዓቶቹም፣ 1ኛ. 25 በመቶ የኑግ ፋጉሎ +74 በመቶ የስንዴ ፉርሽካ +1 በመቶ የጨው ቅልቅል ሆኖ 18 በመቶ፣ 2ኛ. 38.5በመቶ የኑግ ፋጉሎ +60.5 በመቶ የስንዴ ፉርሽካ +1 በመቶ የጨው ቅልቅል ሆኖ 20 በመቶ፣ 3ኛ. 29 በመቶ የተልባ ፋጉሎ +70 በመቶ የስንዴ ፉርሽካ +1 በመቶ የጨው ቅልቅል ሆኖ 18 በመቶ፣ 4ኛ. 43 በመቶ የተልባ ፋጉሎ +56 በመቶ የስንዴ ፉርሽካ + 1 በመቶ የጨው ቅልቅል ሆኖ 20 በመቶ፣ 5ኛ. 27 በመቶ የጥጥ ፋጉሎ +72 በመቶ የስንዴ ፉርሽካ + 1 በመቶ የጨው ቅልቅል ሆኖ 18 በመቶ፣ 6ኛ. 40 በመቶ የጥጥ ፋጉሎ +59 በመቶ የስንዴ ፉርሽካ +1 በመቶ የጨው ቅልቅል ሆኖ 20 በመቶ የሰውነት ገንቢ ንጥረ ነገር (ክሩድ ፕሮቲን) ይዘት ያላቸው ነበሩ፡፡ 20በመቶ ክሩድ ፕሮቲን  ይዘት ያለው የጥጥ ፋጉሎ የተካተተበትን የድጎማ መኖ የተመገቡት ወይፈኖች በ1 ዓመት ዕድሜያቸው በአማካይ 196.50 ኪ.ግ፣ በ2 ዓመታቸው ደግሞ 404.88 ኪ.ግ መመዘን ችለዋል፡፡ በሌላ መልኩ 18 በመቶ ክሩድ ፕሮቲን ይዘት ያለው የተልባና የጥጥ ፋጉሎ የተካተተበትን የድጎማ መኖ የተመገቡት ወይፈኖች በ1 ዓመታቸው 162.50 ኪ.ግ፤በ2 ዓመታቸው ደግሞ 314.25 ኪ.ግ መመዘን ችለዋል፡፡ እንዲሁም 20 በመቶ ክሩድ ፕሮቲን  ይዘት ያለው የጥጥ ፋጉሎ የተካተተበትን የድጎማ መኖ የተመገቡ 50 በመቶ የሆልስቴን ፍሬዥያን ደም ያላቸው ወይፈኖች 75በመቶ የሆልስቴን ፍሬዥያን ደም ካላቸው ወይፈኖች የተሻለ የቁም ክብደትና የቀን ዕድገት ያሳዩ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ቀደም ብሎ የተጠቀሰውን የድጎማ መኖ ተመግበው የደለቡ 50በመቶ የሆልስቴን ፍሬዥያን ደም መጠን ያላቸው ወይፈኖች በአማካይ 10792.70 ብር፣ ተመሳሳይ የፕሮቲን ይዘት ያለው የተልባ ፋጉሎ የተካተተበትን የድጎማ መኖ ተመግበው የደለቡ ተመሳሳይ የደም መጠን ያላቸው ወይፈኖች ደግሞ 5772.60 ብር በከብት የተጣራ ገቢ የሚያሰገኙ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ የወተት ከብት አርቢዎች በዕርባታቸው የሚወለዱ ወይፈኖችን፤ በተለይም 50 በመቶ የሆልስቴን ፍሬዥያን ደም ያላቸውን ወይፈኖች 20 በመቶ የፕሮቲን ይዘት ያላቸውን የጥጥና የተልባ ፋጉሎዎች የተካተቱባቸውን የድጎማ መኖዎች እየመገቡ በማደለብ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡


 


Abstract


The study was conducted at Holetta Research Center to evaluate growth performance and economic feasibility of fattening 50 and 75% Friesian-Boran growing crossbred bull calves for the period of 626 days. Twenty-four 50% Frisian-Boran crossbred weaned male calves and another twenty- four 75% Frisian-Boran crossbred growing weaned calves reared at Holetta Research Center were randomly assigned to six dietary treatments; T1=Noug seed cake based supplement with  18% CP level, T2=Noug seed cake based supplement with 20% CP level, T3= Linseed cake based supplement with 18% CP level, T4= Linseed cake based supplement with  20% CP Level, T5=Cottonseed cake based supplement with 18% CP and T6=Cottonseed cake based supplement with 20% CP Level. The interaction effect between feed supplements and calf genotypes was not significant. In this study higher (p<0.05) body weight of 196.50±7.78 and 404.88±17.96 kg was attained for 12 and 24-months growing bull calves that were supplemented with cotton seed cake at 20% crude protein level, respectively than calves supplemented with 18% CP level. Crossbred bull calves supplemented with cotton seed cake at 20% CP had also higher (p<0.05) final body weight, live weight change, daily weight gains and feed conversion efficiencies of 404.88±17.96, 334.25±17.62, 0.558±0.03 kg and 9.46±0.87 kg DMI/kg gain, respectively than those fed on noug seed cake at 18% CP level (314.25±17.96, 244.25±17.62, 0.407±0.03 kg and 13.60±0.88 DMI/kg gain), respectively. Except for initial weight, i.e., weaning weight and feed conversion efficiencies, Friesian-Boran (50% FB) crossbred growing bull calves had better (p<0.05) final body weight, live weight change and daily weight gain of 378.04±17.96, 308.79±10.17 and 0.518± 0.02, respectively compared to those with 75% exotic blood level (346.25±10.37, 275.38±10.17, and 0.463.02) respectively. Friesian Boran (50% FB) crossbred growing bull calves fed on cotton seed cake-based supplement with 20% CP level (T6) had better net income of 10792.7 ETB/head followed by those supplemented with linseed cake with 20% CP level (T4) which was 5772.6 ETB/head. Generally, dairy producers (farmers) can benefit from fattening of their crossbred dairy bull calves; especially 50% Friesian-Boran crosses using Cotton and linseed cakes-based concentrates formulated with 20% crude protein.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605