Main Article Content

Farmers’ Maize Variety Ranking as a Food-Feed Crop and the Influence of the Feed Attribute on Variety Preference in Selected Mixed Crop-Livestock Production Areas of Ethiopia


Ashenafi Mengistu

Abstract

አህፅሮት


የሕዝብ ቁጥር መጨመር በግጦሽ መሬት ይዞታ ላይ በሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ምክንያት እንስሳት ለመኖ ምንጭነት በሰብል ተረፈ ምርቶች ላይ የበለጠ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል:: በቅይጥ ሰብል ምርትና እንስሳት ርባታ ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች የበቆሎ ዝርያን የመኖነት ጠቀሜታ ከዝርያ ምርጫ መመዘኛዎች አንዱ አድርገው እንደሚወስዱ የሚሰጥ መላምት አለ፡፡ የአሁኑ ጥናት ዓላማ የአርሶ አደሩን የበቆሎ ዝርያ ምርጫ ከሰብል ምርት በተጨማሪ የመኖነት ጠቀሜታን (ፖቴንሻል ዩቲሊቲ ኢንዴክስን) እንደመመዘኛ ይወስዳሉ የሚለውን መላምት ለመመርመር ነው፡፡ የዝርያ ምርጫ መረጃዎች በሞዴል (መልቲኖሚያል ሎጂት) በመታገዝ የተተነተኑ ሲሆን በውጤቱም BH 660 የተባለው የበቆሎ ዝርያ በሰብል ምርታማነቱ፣ በገለባ ምርቱና በገለባ የመኖነት ጠቀሜታው በአርሶ አደሮች የላቀ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ በተያያዘ የአባወራው/የእማወራዋ የትምህርት ደረጃ፣ የግብርና ስራ ልምድ፣ የቤተሰብ ብዛት፣ የእርሻ መሬት ይዞታ፣ የእንስሳት ባለቤትነት፣ የብድር አቅርቦት፣ የግብርና ስርፀት አገልግሎት እና ፖቴንሻል ዩቲሊቲ ኢንዴክስ በአርሶ አደሮች የበቆሎ ዝርያ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ የዚህ ጥናት ውጤት በጥቅሉ በቅይጥ ሰብል ምርትና እንስሳት ርባታ የግብርና ስርዓት ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች የተሻሻሉ የበቆሎ ዝርያዎችን ሲመርጡ የመኖነት ጠቀሜታቸውንም ከግምት ውስጥ ያስገባሉ የሚለውን መላምት የሚደግፍ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተጨማሪም ውጤቱ እንስሳት የሚያረቡ በቆሎ አምራች አርሶ አደሮች የተሻሉ የመኖነት ባህሪያትን ከሰብል ምርታማነት ጋር አዳቅለው የያዙ የበቆሎ ዝርያዎችን እንደሚመርጡ በተጨባጭ አሳይቷል፡፡  


 


Abstract


The ever increasing population pressure with subsequent dwindling grazing land area pushes greater dependence of livestock on crop byproducts as feed source. There is a hypothesis that maize producers in the mixed farming system value the feed attribute of maize varieties for adoption. This study was conducted to investigate farmers’ rankings of maize varieties as a food-feed crop and analyze the influence of the feed attribute as described by the potential utility index in addition to grain production. The preference data generated from the study were fitted to a multinomial logit model. Results of the ranking exercise showed that BH660 was the highest in grain, stover and digestible stover yields whereas it was least in terms of palatability followed by BH540. Socio-economic variables which included education level of the household head, farming experience, family size, farm size, livestock ownership, access to credit and access to extension service, and the variety attribute - potential utility index (PUI) - influenced farmers’ maize variety preference. The results generally support the hypotheses set regarding factors that influence farmers’ preference to improved maize varieties. Moreover, strong indications that livestock owning farmers do show preference to maize varieties that are with desirable stover characteristics for feeding livestock in addition to grain yield were evident.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605