Main Article Content

Effect of Phosphate-Solubilizing Bacteria and Fungi, Mineral Phosphate and Vermicompost Application on Major Soil Chemical Characteristics, Mineral Uptake and Growth of Coffee (Coffea arabica L.) Seedlings under Nursery Condition


Reshid Abafita
Fasil Asefa
 Diriba Muleta
 Diriba Muleta

Abstract

አህፅሮት


 ይህ ጥናት የተዘጋጀው የባክቴሪያ እና የፈንገሶች ፎስፌት ማዳበሪያ ቀማሪነትና የአሟሚነት ብቃታቸውን መገምገም፣ የቡናን ምርታማነት አመላካች ባህርይ በሆነው የቡና ችግኝ ዕድገት ላይ በቡና ችግኝ ማፊያ ጣቢያ ደረጃ መፈተሽና አጅግ በጣም ጥሩ ብቃት ያሳዩትን መምረጥ ነበር። ጥናቱ የተከናወነው ከየካቲት እስከ ነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም. በጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል የቡና ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ በመጠቀም ነበር። ይህ ሙከራ የተከናወነው ፍፁም በዘፈቀደ አሠራር እያንዳንዱን ተጠኝ በሶስት ቅጅ በመደጋገም ነበር። ሙከራው 4 ስብስቦች ነበሩት፣ 1ኛው ስብስብ ሁለት ምድብ ያለው ፎስፌት ማዳበሪያ አሟሚ ባክቴሪያና ፈንገሶች ምድብ እና ፎስፌት ማዳበሪያ ከፎስፌት አሟሚ  ባክቴሪያና ፈንገሶች ጋር የተጣመረ ምድብ፣ 2ኛው ስብስብ 3ባክቴሪያዎችና 3ፈንገሶች እና ሁለት ደረጃ ያለው ፎስፌት የተጣመረበት፣ 3ኛው ስብስብ በነጠላ 6ቱ ፎስፌት ቀማሪ ባክቴሪያና ፈንገሶች 1.5 ኪ.ግ አፈር ከ300ግራም ቨርሚኮምፖስት ጋር የተደባለቀ፤ 3ኛው ስብስብ ባለ2 ፋክቶሪያል ሙከራ ሆኖ (3 ደረጃ ያላቸው ፎስፌት ቀማሪ ባክቴሪያና ፈንገሶች እና 3 ደረጃ ያላቸው ፎስፌት ቀማሪ ባክቴሪያና ፈንገሶች ከቨርሚ ኮምፖስት ጋር የተጣመረበት) ነበር። ሁሉም የሙከራ ስብስቦች ነጋቲቭ እና ፖዘቲቭ ማነፃፀሪያ የነበራቸው ሲሆን ስብስብ 3 እና 4 በተጨማሪ ቨርሚኮምፖስት ብቻውን እንደማነፃፀሪያ  ነበራቸው። ባክቴሪያና ፈንገሶችፎስፈት ማዳበሪያ ጋር ሲጣመሩ የላቀ ትርጉም ያለው በተክሎች ዕድገት ላይ አሳይቷል። በተጨማሪም RSCF1.19 ከ3ቱ ባክቴሪያዎች (RCHVCB1, RScB1.19, RMaB2.11) ጋር ተዋህደው በአንድ ላይ ፎስፌት ማዳበሪያ ጋር ሲዘሩ በቡና ችግኝ ዕድገት ላይ እጅግ የላቀ ውጤት ተመዝቧል በአጠቃላይ አብላጫ ያለው የተክሎች ዕድገት ባህሪይ መለኪያ የሆኑ ነገሮች በነጠላና በጥምረት አጨማመር ጊዜ ከቨርሚኮምፖስት ጋር በመጣመሩ ምክንያት ከነገቲቭና ፖዘቲቭ ማነፃፀሪያ ጋር ሲወዳደር ጭማሪ ዕድገት አሳይቷል በጥቅሉ ትርጉም አዘል ውጤት ያልሆነ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ N,P እና K አጠቃቀም በተፈጥሮ ማዳበሪያ ቀማሪ ባክቴሪያ፣ ፈንገሶችና ሰው ሰራሽ ፎስፌት ማዳበሪያ ጥምረት ጊዜ ከነገቲቭና ፖዘቲቭ ማነፃፀሪያ ጋር ሲወዳደር ብልጫ ያለው ውጤት ተመዝግቧል ቨርሚኮምፖስት RSCF1.19  እና RLVCF2 ፈንገሶች ጋር ሲጣመሩ እጅግ የገዘፈና ጤናማ የሆነ የአረቢካ ቡና ችግኝ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አፈር ላይ ለማሳደግና ለማምረት የተመረጠ ሆኖ ተገኝቷል።


 


 


Abstract


 This study was designed to evaluate the efficiency, select the best performing bacteria and fungi isolates for phosphate solubilization, and yield attributes of coffee seedlings under nursery conditions. The study was conducted at Jimma Agricultural Research Center from February to August 2019, in plastic pots. This study was carried out in CRD in three replications per treatment. The experiment has 4 sets where set 1 had the bio-inoculant factors and phosphate factor combined factorially. Set 2 had 3 factors (3PSF, 3PSB, and 2 p levels) in factorial combinations. Set 3 has a single factor (the 6 inoculants under basal VC (300g/1.5kg soil). Set 4 was a two factor trial: PSF (3 levels) and PSB (3 levels) combined factorially under basal VC. All sets had negative and positive (rec. NP) controls, and set 3 and 4 had sole VC as the additional control unit. Bio-inoculant and phosphate combination were significantly responded to all growth attributes. Moreover, co-inoculation of RSCF1.19 with three bacterial isolates (RCHVCB1, RScB1.19, and RMaB2.11) in combination with phosphate led to significantly higher tested growth parameters. A similar increase in growth attributes was observed in both single and dual inoculation due to VC used when compared with both positive and negative control. Non-significant but higher NPK-uptake was observed in a combination of bio-inoculants and phosphate fertilizer compared to the positive and negative control. The combination of VC with RSCF1.19 and RLVCF2 fungal isolates can be recommended as bio-inoculants for solubilizing inorganic phosphate and to obtain vigor and healthier coffee seedlings in the southwest soil of Ethiopia for coffee Arabica cultivation.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605