Main Article Content

Technical Efficiency of Lowland Rice Production in Northwest of Ethiopia


Abebaw Assaye
Mesay Yami
Shewaye Abera

Abstract

አህፅሮት

ለዚህ ጥናት ኮብ ዳግላስ ስቶካስቲክ ፍሮንታየር ፕሮዳክሽን ፋክሽን የተባለውን የመረጃ ትንተና ዘዴ በመጠቀም በአማራ ክልል የፎገራ ወረዳ ሩዝ አምራች የሆኑ አነስተኛ አርሶ አደሮችን የሩዝ አመራረት ሙያዊ ብቃት ደረጃና ሙያዊ ብቃታቸው ላይ ተጽንኦ የሚያደርሱትን የመለየት ስራ ሰርተናል፡፡ ለዚህ ጥናት 202 ሩዝ አምራች አርሶ አደሮችን በእጣ በመለየት በ2008/09 የምርት ዘመን መረጃዎችን ተጠቅመናል፡፡ የጥናቱ ውጤት  እንደሚያሳየው የአርሶ አደሮች አማካይ የሩዝ አመራረት ሙያዊ ብቃት  ደረጃ 85 መቶኛ ሲሆን ዝቅተኛና ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት ደረጃም 22 እና 99 መቶኛ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ አነዚህ አርሶ አደሮች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ቢሰሩ የሩዝ ምርታማነትን አሁን ካለው 3.2 ቶን በሄክታር ወደ 3.7 ቶን በሄክታር ማሳደግ ይቻላል፡፡ ስለሆነም የአርሶ አደሮችን ሩዝ የማምረት ሙያዊ ብቃታቸውን በማሻሻል የሩዝ ምርታማነትን ለማሳደግ ወደፊት ትኩረት ተሠጥቶ ሊሰራ ይገባል፡፡ይህም ሊሳካ የሚችለው የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠርና በቂ የምርምርና ኤክስቴንሽን ድጋፍ ለአርሶ አደሮቻችን በመስጠት ነው፡፡

 

Abstract

This study employed the Cobb-Douglas stochastic frontier production function to measure the level and determinants of technical efficiency of smallholder rice producers in the Fogera district of Amhara Region, Ethiopia. A multistage sampling procedure was used to select 202 rice producers sample farmers in 2016. The result of the analysis showed that the mean technical efficiency was 85 %, with a minimum and maximum efficiency level of about 22% and 99%, respectively. By operating at full technical efficiency levels, rice productivity could increase, on average, from the current 3.2 tons ha-1 to 3.7 tons ha-1. Therefore, the future direction should trigger towards enhancing rice productivity per hectare by improving technical efficiency at the farm level in addition to technological progress. Efficiency gains could be realized by designing better institutional support, improving soil fertility, focusing on livestock production and ensuring an adequate provision of research and extension support to rice farmers.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605