Main Article Content

Aflatoxin Contamination of Ethiopian Hot Red Pepper and Risk Characterization: Dietary Exposure Assessment and Estimated Aflatoxin-Induced Hepatocellular Carcinoma


Tariku Hunduma
Antenen Tesfaye
 Melaku Alemu

Abstract

አህፅሮት


በምግብ ሰንሰለት ውስጥ በምግብ ወለድ ሻጋታዎች የሚመነጩ የተለያዩ መርዛማ ኬሚካሎች በሰው ጤና፣ በምግብ ንግድና በኢኮኖሚ ላይ  ከፍተኛ ጫና ያስከትላሉ፡፡ ይህ ጥናት በበርበሬ ድህረ-ምርት የምግብ ሰንሰለት ሂደት ላይ በሻጋታዎች ሊመነጩ የሚችሉ አፍላቶክሲን የሚባሉ መርዛማ ኬሚካሎች ብክለትን፣ የሰው ተጋላጭነትንና ሊከሰት የሚችሉ ተዛማች የጤና ጠንቆችን ገምግሟል፡፡ በአጠቃላይ በ25 ድብልቅ የላቦራቶሪ ናሙናዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ በ48 ከመቶ ናሙናዎች ውስጥ አፍላቶክሲን ተገኝቷል፡፡ አፍላቶክሲን ጅ1 (aflatoxin G1) የሚባለው የአፍላቶክሲን ዓይነት በከፍተኛ ድግግሞሽና መጠን የተገኘ ሲሆን  አፍላቶክስን  ቢ1 (aflatoxin B1) የተባለው ደግሞ በተከታይነት ተመዝግቧል፡፡ በዚህ ጥናት  ወቅት ከፍተኛ የአፍላቶክሲን መጠን (ማግ/ኪግ) (43.61 አፍላቶክስን  ጅ1 እና 22.18 አፍላቶክስን  ቢ1) ከታሸጉ የበርበሬ ዱቄት ናሙናዎች ሲመዘገብ በተከታይነት ካልታሸጉ የበርበሬ ዱቀት ናሙናዎች (30.53 አፍላቶክሲን  ጅ1  እና 13.50 አፍላቶክሲን  ቢ1) ተመዝግቧል፡፡ አፍላቶክስን  ከተገኙባቸው ናሙናዎች ውስጥ 42 በመቶ በአፍላቶክሲን  ቢ1 ይዘታቸው ከአውሮፓ ሀገራት የደህንነት ደረጃ (5 ማግ/ኪግ) በላይ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ አፍላቶክሲን በድግግሞሽ፣ በዓይነትና በመጠን በምግብ ሰንሰለቱ ሂደት ከታች ወደ ላይ የመጨመር እዝማሚያ አሳይቷል፡፡ በዚህ ጥናት አንድ ሰው በአማካይ በቀን 1.04 ናግ አፍላቶክሲን  በ1/ኪግ የሰውነት ክብደት የሚወስድ ሆኖ የተገኘ ሲሆን በዚህ መጠን 0.0188, 0.0098 እና 0.0286 የጉበት ካንሰር ክስተት/ዓመት/100,000 ሕዝብ በሄፓታይትስ ቢ  ፖዘቲቭ፣ ኔጋቲቭ  እና ጎልማሳ ማህበረሰብ እንደ አጻጻፉ ቅደም ተከተል ሊከሰት እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ይህ የካንሰር ክስተት አንዳንድ ድርጅቶች ባስቀመጡት የካንሰር ክስተት ደረጃ መጠን (1 በ100,000 ካንሰር) ሲታይ እምብዛም አሳሳቢ አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ ጥናት በአንድ የምግብ ዓይነት ብቻ ላይ የተሰራ ከመሆኑም በላይ የአፍላቶክስን  ስርጭት ከዓመት ወደ ዓመት እና ከቦታ ወደ ቦታ የሚለያይ ስለሆነ የዚህ ጥናት የካንሰር ክስተት ውጤት እንደ ደህንነት መተማመኛ ሊወሰድ  አይገባም፡፡ በተጨማሪ የተጋላጭነት ጥናቱ በብዙ የምድብ ዓይነት ላይ ቢሰራ ሊከሰት የሚችለው የጤና ጠንቅ ከዚህ ሊብስ ይችላል፡፡ እንደ ማጠቃለያ የአፍላቶክሲን በድግግሞሽ፣ በዓይነትና በመጠን በምግብ ሰንሰለቱ ሂደት እየመጨረ የመሄድ እዝማሚያ አፍላቶክሲኑና ተዛማች የጤና ጠንቁ ምግቡ ለምግብነት እስከሚቀርብበት ድረስ ሊኖርና ሊከሰት እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡ ስለዚህ አፍላቶክሲን አንድ ጊዜ በምግብ ውስጥ ከመነጨ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ አዳጋች በመሆኑ ቅድመ የመከላከል ዘዴን በምግብ ሰንሰለት ላይ አትኩሮ መስራት ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል፡፡


 


 Abstract


Aflatoxins are toxic fungal secondary metabolites, and their presence in the food chain can cause adverse health effects, impair trade and pose a significant economic burden. This study analyzed aflatoxin contamination along a hot pepper postharvest value chain, estimated its dietary exposure and its associated potential health risk to consumers. A total of 25 composite samples were analyzed for aflatoxins using immunoaffinity column cleanup and HPLC. Aflatoxins were detected in 48 % of the tested samples. Aflatoxin G1 was recorded at highest frequencies and contamination levels followed by AFB1. Uppermost contaminations (µg/kg) were recorded from packed pepper powder (43.61 AFG1 and 22.18 AFB1) followed by unpacked pepper powder (30.53 AFG1 and 13.50 AFB1). Five (42 %) of the positive samples exceeded the EU regulatory limits for AFB1 (> 5 µg/kg). Aflatoxin detection frequencies, aflatoxin types and contamination levels generally increased up along the chain. The mean daily intake dose was found as 1.04 ng AFB1/kg bw/day and the cancer risk was estimated to be 0.0188, 0.0098 and 0.0286 cancer cases/year/100,000 population of hepatitis B surface antigen positive, negative and adult subpopulation, respectively. This cancer risk level can be considered “essentially negligible” as compared to 1 x 10-5 cancer risk level established by some agencies. However, as this study was dependent on a single food commodity, and aflatoxin contamination level varies from year to year and location to locations, the risk level of this study should not be taken as assurance for safe risk level. In addition, if aggregate dietary exposure is considered, possible health risk would be high. In conclusion, the increased trends of detection frequencies, aflatoxin types and contamination levels up along the value chain signified the possible occurrence of the toxin and their associated health risk as the food commodity approaches consumption. Because complete elimination of aflatoxin is almost unachievable once contamination has happened, preventative management efforts should target the value chain.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605