Main Article Content

Performance Evaluation of Engine Operated Potato Grader


Dereje Alemu
Abebe Fanta
Bisrat Getnet

Abstract

 አህፅሮት


ድንችን በባህላዊ መንገድ በመጠን የመለየት ስራ ብዙ ሰዓትና የሰው ጉልበት የሚፈልግ በጣም አድካሚና አነስተኛ ውጤት የሚያስገኝ ስራ ነው። ስለሆነም ድንችን ወደ ተለያየ መጠን የሚለይ በሞተር ኃይል የሚሰራ ማሽን ፍተሻ እና የመገምገም ስራ ተሰርቷል። የመለያ ማሽኑ በተለያየ መጠን የሚለየውን ድንች ማስገቢያ፣መለያ ሲሊንደር፣ኃይል ማስተላለፊያ ዘንግና መቀበያ አሉት። ሙከራው በተለያየ ጡዘት (10፣15 እና 20 ጡዘት በደቂቃ)፣ ዘዌ (5፣10 እና 15 ዲግሪ) እና በተለያየ የድንች አጨማመር በደቂቃ (20፣ 30 እና 40ኪ.ግ) በስፕሊት ስፕሊት ፕሎት የሙከራ ዲዛይን (split split plot design)ተከናውኗል። የማሽኑን የድንች የመለየት አቅም፣ የመለየት ስርዓት ውጤታማነት፣የነዳጅ ፍጆታ እና መካኒካዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት የመገምገም ስራ ተከናውኗል። የፍተሻ ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት የማሽኑ የመለየት አቅም እና የነዳጅ ፍጆታው የመለያ ሲሊንደሩ ፍጥነት እና የሚለየው የድንች መጠን ሲጨምር አብሮ የሚጨምር ሲሆን የድንች ሜካኒካዊ ጉዳት እና የመለየት ስርዓት ውጤታማነት ደግሞ የዘዌ መጠን ሲጨምር እየቀነሰ ይሔዳል። ከፍተኛው የማሽኑ የመለየት ስርዓት ውጤታማነት የተገኘው ማሽኑ በ15 ጡዘት በደቂቃ እና በ5 ዲግሪ ዘዌ፤ 20 እና 30 ኪ.ግ. በደቂቃ ድንችን በተለያየ ጊዜ በመጨመር በሚለይበት ጊዜ 97.57 እና 97.67% በቅደም ተከተል ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ የድንች መለያ ማሽን የኢኮኖሚ አዋጭነቱ ተጠንቶ በሀገር ውስጥ አምራቾች ተባዝቶ ለተጠቃሚዎች ቢቅርብ የድንች አምራቾችና በምርት እሴት ሰንሰለት ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን ውጤታማነትን ያሳድጋል።


Abstract


 Traditional methods of grading potato tubers require high labor-hour, cause fatigue to workers, and have low output. Hence, an engine-driven machine capable of grading potato tubers into different size classes was evaluated. The grader prototype consisted of a feeding table, grading cylinder, and catchment tray. Grading capacity, grading system efficiency, mechanical damage, and fuel consumption were used to determine the performance of the machine. Split-split-plot experimental design where grading cylinder speeds (10, 15, 20 rpm) were the main plots, angle of inclinations (5, 10, and 15°) as sub-plots, and feeding rates (20, 30, 40 Kg.min-1)as sub-sub-plots with three replications were used. The results indicated that grading capacity and fuel consumption increased with increasing cylinder speed and feed rate while percentage mechanical damage and grading system efficiency decreased with increasing angle of inclination. The maximum grading system efficiency of 97.57% and 97.67 % was observed when the machine was operated at speed of 15rpm, angle of inclination of 5°, and feed rate of 20 and 30 kg.min-1, respectively. From the performance indices, it can be concluded that the performance of the machine is very much acceptable with a high prospect for extending the technology for small and medium-scale farmers and potato whole sellers along the value chain.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605