Main Article Content

Farmer Preferred and Financially Feasible Onion Varieties for Scaling: Evidence from the Central Rift Valley in Ethiopia


Fistum Miruts
Bedru Beshir
Gadissa Ejersa

Abstract

አህፅሮት


ሽንኩርት በኢትዮጵያ በዋነኛነት በሞቃት ወራት፣ በቆላና በወይና ደጋ የሚመረት አትክልት ነው፡፡ የሰብሉን ምርታማነት በተመለከተ አርሶ አደሩ በአማካይ ከአንድ ሄክታር የሚያገኘው ምርት በምርምር ማሳ ላይ ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም የተሻሻሉ የሽንኩርት ዝርያዎችን በሰርቶ ማሳያ ማስተዋወቅና ተሳትፏዊ ግምገማ በማድረግ በአዳማ፣ በሉሜ እና በአዳሚቱሉ ጂዶኮምቦልቻ ወረዳዎች ከአርሶ አደሮች ጋር በማሳቸው ላይ ተካሂዷል።  ሰላሳ ሰባት የሽንኩርት አምራች አርሶ አደሮች 9.25 ሄክታር ላይ የሰርቶ ማሳያ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ናፊስና ናሲክ ሬድሽንኩርት ዝርያዎች ከቦምቤይ ሬድ (ማነፃፀርያ) ጋር ለማወዳደር ተችሏል፡፡ በዚህም በአማካይ ናፊስና 29757 ./ እና ናሲክ ሬድ 27676 ./ ምርት ተመዝግቧል፡፡ ይህ የምርት ዉጤት ከማነፃፀሪያው ዝርያ ጋር ሲወዳደር 924 ./ እና 693 ./ ጭማሪ አለው፡፡ የገንዘብ ትርፋማነትን ስንመለከትም ናፊስ ዝርያን ማምረት የበለጠ አዋጭ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ናፊስ በአርሶ አደሩ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ለዚህም መመዘኛው ከፍተኛ ምርት፣ ደማቅ ቀይ ቀለም፣ መካከለኛ ኮረት፣ ከፍያለ የበሽታ መቋቋም አቅም፣ ጥሩ መዓዛ በገበያ ተመራጭነት  እና ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት ከናሲክ ሬድ እና ቦምቤይ ሬድ ጋር ሲወዳደር በጣም ጥሩ የሽንኩርት ዝርያ ሆኖ ተመርጧል፡፡ በመሆኑም የሽንኩርት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ናፊስና ናሲክ ሬድ ዝርያዎች ይህ ጥናት በተካሄደባቸው ቦታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የግብርና ስነ-ምህዳር ያላቸው አካባቢዎች የሚመለከታቸው የግብርና ልማት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በማስፋፋት የሽንኩርትን ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል እንመክራለን፡፡


 


 


 


Abstract


Onion is a warm-season vegetable crop grown in Ethiopia. The productivity, however, is low on farmers' fields as compared to its recorded potential yield on the research station. So, participatory on-farm demonstration and evaluation of improved onion varieties with their associated production practices were conducted in Adama, Lume, and Adamitulu-Jidokombolcha (AJ) districts in the Central Rift Valley area.  Nafis and Nasik Red were compared with Bombay Red, the check. Thirty-seven onion grower farmers were purposely selected and hosted the demonstrations on 9.25 hectares. Nafis and Nasik Red performed higher than the check yielding 29,757 kg/ha and 27,676 kg/ha on average respectively. The farmer-based practices yield gap was found to be 9,238 kg/ha and 6,931 kg/ha for Nafis and Nasik Red respectively. Given, equal investments per unit area to produce the onion varieties, Nafis gave higher profit. Similarly, Nafis was the most preferred onion variety compared to Nasik Red and Bombay Red because of its higher yield, deep red color, medium bulb size, tolerance to disease, pungency, market preference, and longer shelf life. Nafis and Nasik Red produced higher financial returns and were preferred by farmers. Hence, the varieties need wider scaling through concerted efforts of agricultural development partmets in the study area and in similar agro-ecologies to enhance onion production and productivity in Ethiopia.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605