Main Article Content

Role of Sugarcane Tops as Feed Resource in Two Sugar Estates of Central Ethiopia


Getahun Kebede

Abstract

አህፅሮት


የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ከወንጂና መተሃራ ስኳር ፋብሪካዎች የሚገኘው የሸንኮራ አገዳ ጫፍ ለእንስሳት አርቢዎች ያለውን የመኖ ጠቀሜታ ዳሰሳን መሠረት ያደረገ ነበር፡፡ ጥናቱም በስኳር ፋብሪካዎች አከባቢ ባሉ ከተሞች፤ ካምፖችና ቀበሌ ገ/ማህበራት የሚገኙ 308 እንስሳት አርቢ አባወራዎችን ለቃለ መጠይቅ ያሳተፈና ከፋብሪካዎች የተገኘን መረጃ ያካትታል፡፡ በጥናቱ የሸንኮራ አገዳ ጫፍ የምርት መጠን ፤ የመኖ ጠቀሜታው፤ አያያዝና አመጋገብ ልምድ፣ ግብይት እና የአጠቃቀም ችግሮች ተዳሰዋል፡፡ ከየፋብሪካው ማሳ በዓመት የሚገኛው የሸንኮራ አገዳ ጫፍ መጠን በዓመቱ ለስኳር ምርት ሲባል ታጭዶ ከሚፈጨደው የሸንኮራ አገዳ መጠን ጋር ቀጥተኛ ተዛማጅነት አለው፡፡ በዓመታዊ ምርት መጠን በእሳት የተለበለበው የአገዳ ጫፍ ካልተለበለበው የአገዳ ጫፍ ይበልጣል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ለስኳር ምርት የሚውለው ሸንኮራ አገዳ ከመቆረጡ በፊት ማሳው እሳት የምለቀቅበት በመሆኑና ያልተቃጠለው የአገዳ ጫፍ የሚገኘው በአገዳ ተከላ ወቅት ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ የሸንኮራ አገዳ ጫፍ በሁሉም አባወራዎች (100%) እንስሳት መኖነት ከመዋሉም በላይ ለማገዶና (50%) ለግንባታ ሥራዎች (37%) ያገለግላል፡፡ በአቅርቦትና በመኖ ተፈላጊነት ረገድ በእሳት የተለበለበ (የተቃጠለ) ሸንኮራ አገዳ ጫፍ በእሳት ካልተለበለበው የአገዳ ጫፍ ብልጫ ያለው ሲሆን ይህም የመኖ እጥረት በሚታይበት ደረቅ ወራት አማራጭ የመኖ ግብዓት ነው፡፡ የሸንኮራ አገዳ ጭፍ በከተማ ለሚገኙ ከብት አርቢዎች በግለሰቦች አመካኝነት በሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ዋጋውም በስኳር ፋብሪካው፤ በአገዳው ዓይነትና በቦታው (ማሳ) ርቀት ይለያያል፡፡ በእሳት ካልተለበለበው አገዳ ይልቅ የተለበለበው አገዳ እንደዚሁም ከወፍራም አገዳ ይልቅ ቀጫጭን አገዳ ያላቸው ዝሪያዎች ለእንስሳት መኖነት የበለጠ ተፈላጊ ናቸው፡፡ የሸንኮራ አገዳ ጫፍ በአብዛኛው ለእንስሳት የሚሰጠው ባለበት ሁኔታ ወይም በመጠኑ በመቀረጣጠፍ ሲሆን የተሰበሰበውም በበቂ ሁኔታ ሳይደርቅ በውጪ ይከማቻል፡፡ የሸንኮራ አገዳን ለእንስሳት መኖነት በይበልጥ ለመጠቀም የማያስችሉ ዋንኞቹ ማነቆዎች የመኖ ይዘቱ ደካማ መሆን (91.2%)፤ የቴክኒክ ድጋፍ እጦት (89%)፤ የማጓጓዣ እጥረት (26%)፤ በተመጋቢ እንስሳት ላይ የአፍ መቁሰል ችግር (16.2%) እና የሰው ጉልበትና ካፒታል እጥረት (11.7%) ናቸው፡፡ በመሆኑም በሸንኮራ አገዳ ጫፍ አጠቃቀም፣ ጥራት ማሻሻል፣አያያዝ፤አመጋገብ ዘዴዎችና ግብይት ላይ ለአርቢዎች በቂ ተግባር-ተኮር ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪም የሸንኮራ አገዳ ጫፍን ለመቀርጠፍ የሚያግዝ ማሽን (ቾፐር) በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርቢዎች ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡


 


Abstract


This study aimed to assess the production and utilization of sugarcane tops (SCTs) by livestock farms in and around Wonji-Shoa and Metehara sugar estates. A total of 308 households were interviewed using a semi-structured questionnaire, where data on household characteristics and acquisition, utilization, feeding practices, preserving, and marketing of SCTs were collected. Secondary data on sugarcane production were taken from the sugar factories. The estimated production of SCT is proportional to the volume of sugarcane produced or milled and the area of sugarcane field harvested, which was higher in Metehara compared to Wonji-Shoa sugar estate. The volume of burnt SCTs surpassed that of green SCTs as the pre-harvest burning practice of sugarcane fields favors the abundant availability of the former. Sugarcane tops were used as feedstuff by the entire surveyed households, primarily for ruminants feeding. Besides, a significant proportion of farmers reported using SCTs for other purposes viz. fuel source (50%) and construction (37%). Availability and feed use of the burnt SCT surpassed that of green SCT, mainly during the dry season, or dearth period. Sugarcane tops were sold to urban livestock producers, their price being varied with the sugar estate, SCT type, and distance from the source (field). Farmers preferred the burnt to green SCTs, and thin-stem to thick-stem varieties for livestock feeding. Sugarcane tops were usually fed to animals intact or chopped. Farmers practiced preserving intact SCTs by sun-drying and stored in open-air. Limitations in the feed use of SCTs in the study area included its low quality (91.2%), lack of technical supports (89%), lack of transport (26%), mouth injury on animals associated with feeding unprocessed SCTs (16.2%) and lack of family labor and capital (11.7%). In conclusion, SCTs are available year-round and contribute significantly as livestock feed in the study areas. However, it was poorly utilized due to the harvesting method employed by the industry, poor handling by farmers, and lack of technical supports. Therefore, intervention in areas of SCTs processing, conservation, feeding, and marketing is important to enhance its feed use by livestock farms around sugar industries or beyond.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605