Main Article Content

Seed-Business Oriented Demonstration Trials: An Efficient Option to Promote Tef (Eragrostis tef ) Varieties


Abate Bekele
Solomon Chanyalew
Tebkew Damte
Nigussu Husien
Worku Kebede
Kidist Tolosa
Yazachew Genet
Kebebew Assefa
Demeke Nigussie
Dominik Klauser
Zerihun Tadele

Abstract

አህፅሮት


ኢትዮጵያ ውስጥ ጤፍ (Eragrostis tef) ከ6.5 ሚሊዮን በሚበልጡ አነስተኛ አርሶ አደሮች ይመረታል፡፡ ሆኖም ግን የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችና የምርጥ ዘር ተጠቃሚነት ውስን በመሆኑ የሰብሉ ምርታማነት ዝቅተኛ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ ስለሆነም አነስተኛ አርሶ አደሮች ጥራቱ ለጠበቀ የጤፍ አራቢ ዘር ያላቸውን ተደራሽነት ለመጨመር ዓላማ ያደረገ ጥናት በ254 መሪ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ተካሂዷል፡፡ በጥናቱም በቅርብ ጊዜ የተለቀቁ ሦስት አዳዲስ ዝርያዎች እና አንድ ቀደም ብሎ የተለቀቀ ዝርያ (ቦሰት) ተካተው ተገምግመዋል፡፡ ለእያንዳንዱ መሪ-አርሶ አደር የአራቱም ዝርያዎች ማለትም የኮራ፣ የተስፋ፣ የዳግም እና የቦሰት አራቢ ዘር  ተሰጥቷል፡፡ የአራቱ ዝርያዎች የዘር ምርት ተቀራራቢ (ኮራ = 1.94፣ ተስፋ = 2.31፣ ዳግም = 2.24 እና ቦሰት = 2.36 ቶን በሄክታር) ነበር፡፡ ጥናቱ በተካሄደባቸው ወረዳዎች ያለው የግብዓት ዋጋ እና የምርት ዋጋ እሳቤ ውስጥ ሲገባ የተገኘው አማካይ ያልተጣራ ገቢ 65,355.90 ብር በሄክታር ሲሆን አማካይ የማምረቻ ወጪው ደግሞ 26,355.52 ብር በሄክታር ነበር፡፡ ከማምረቻ ወጪዎች መካከል ለጉልበት የወጣው ወጪ ትልቁን ድርሻ ሲይዝ ከጠቅላላው ወጪ 58 በመቶ ድርሻ ነበረው፡፡ በአጠቃላይ የገቢ-ወጪ ምጣኔ 1.5 በመሆኑ የተሻሻለ የጤፍ ዝርያ ቴክኖሎጂ መጠቀም በጣም ትርፋማ እንደሆነ ጥናቱ መልክታል፡፡ ይህም በመሆኑ አዳዲስ የሚወጡ የጤፍ ዝርያዎችን ዘር አባዝቶ ለገብያ ማቅረብን ትኩረት ያደረገ የሰርቶ ማሳያ ስራ ቢሰራ ለአርሶ አደሮች ሳቢና አዋጭ ሆኖ ተገኝትዋል፡፡


 


ጠቋሚ ቃላት፡ መሪ አርሶ አደሮች፤ የጤፍ ዝርያዎች፤ የምርጥ ዘር ምርት፤ የጤፍ ጭድ፤ የምርት ዋጋ  


 


 


Abstract


Tef (Eragrostis tef) is extensively cultivated by over 6.5 million smallholder farmers in Ethiopia. However, the productivity of the crop remains low mainly due to the limited use of improved technologies including seeds. In this study, three recently released and one old (as a check) tef varieties were evaluated on 254 lead farmers’ fields with the main aim of increasing farmers’ access to quality breed seeds.Each lead farmer was provided with breeder seeds of four improved tef varieties, namely Kora, Tesfa, Dagim, and Boset.The seed yield from the four tef varieties were comparable (Kora = 1.94, Tesfa = 2.31, Dagim =2.24 and Boset = 2.36 t ha-1). Given the input and output prices that prevail in the selected districts, the mean revenue was 65,355.90 Birr ha-1 while the mean production cost was 26,355.52 Birr ha-1. Among production costs, labor took for the lion’s share as it contributed to 58% of the total cost.   In general, with a benefit-cost ratio of 1.5, our technology is highly profitable and attractive to farmers if newly released tef varieties are disseminated in the seed-business-oriented method.


 


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605